ድጋፍና ክትትል የአንድን ተቋም አቅም ለመገንባት...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ድጋፍና ክትትል የአንድን ተቋም አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

ድጋፍና ክትትል የአንድን ተቋም አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡


አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም 


በከንቲባ ጽ/ቤት የተጠሪ ተቋማት   የክትትልና ድጋፍ  ቡድን አባላት የኮሚሽኑን የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራዎች አፈጻጸምን ምልከታ አደረገ፡፡

የድጋፍና ክትትትል ቡድኑ  የዝግጅትና  ተግባር ምዕራፍ እንቅስቃሴ በቸክሊስቱ መሰረት ከገመገሙ በኋላ ቅንጅታዊ አሰራር ላይ  ትኩረት  ሰጥታችሁ መስራት መቻላችሁ የተሻለ ያደርጋችኋል ብለዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ  የዝግጅት ምዕራፍ አጠናቀን የትግበራ ምዕራፍ በገባንበት ወቅት ድጋፍና ክትትል መደረጉ  የታዩትን ክፍተቶች  ለማስተካከል ለ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ስንቅ   ይሆናል ብለዋል፡፡
 
የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ እና የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከንቲባ ጽ/ቤት በዚህ መልኩ የተግባር ምዕራፍ ላያ ያለንን የዕቅድ አፈፃፀም ምልከታ ማድረጉ ለቀጣይ ሥራችን የጎደለንን በመሙላት በተሻለ እንድንፈጽም ያግዘናል ብለዋል፡፡

በድጋፍና ክትትሉ  የተገኙ ዳይሬክቶሬቶችም የተደረገው ድጋፍና ክትትል  ጥንካሬዎቻችን አስቀጥለን  ክፍተቶቻችን  ለማስተካከል  በሙሉ አቅም እንሰራለን ብላዋል፡፡
 
በከንቲባ ጽ/ቤት  የተጠሪ  ተቋማት   የክትትልና ድጋፍ  ቡድን  መሪ አቶ ገለታው ጌታቸው እና የክትትልና  ድጋፍ  ባለሙያ የሆኑት አቶ መሰለ ጌጡ   የሰጠናችሁ ግብረ-መልስ ለቀጣይ ስራዎቻችሁ መሻሻል ይረዳችሁ ዘንድ  ነው ብለው ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments