በመዲናዋ የሚከናወን ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የጤና ስጋት ነው።
በመዲናዋ የሚከናወን ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የጤና ስጋት ነው።
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ ከጤና ስጋትነቱ በተጨማሪ ከተማ አስተዳደሩን በየዓመቱ ከፍተኛ ገቢ ያሳጣዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት፣ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ንግድ ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን መዋቅራቸውን በመያዝ መጭውን አዲስ ዓመትና ሌሎች ብሔራዊ በዓላትን ታሳቢ ባደረገ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ፣ ሥጋ ዝውውር እና የእንስሳት ዝውውርን መከላከል ለከተማዋ ነዋሪ የሚቀርበውን የሥጋ ምርት ጥራት፣ ኃይጅንና ደህንነት ማስጠበቅ በመሆኑ ተቋማት ተቀናጅተን በከፋተኛ ኃላፊነት መስራት አለብን ብለወዋል።
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ዝውውር የሚፈፀመው በአብዛኛው ድብቅ በሆኑ ቦታዎች ስለሚሆን በቅንጅት በጥንቃቄ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ቄራወች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ወ/ሮ ሰናይት መጭውን በዓላት ታሳቢ በማድረግ ጤናማነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት እርድ አገልግሎት ለመስጠት ድርጅቱ በልዮ ሁኔታ ዝግጅት ማደረጉን አስታውቋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የእንስሳት ህገ-ወጥ እርድ እና ዝውውር እንደሚፈጸም ተናግራዋል።
አያይዘውም ህገ-ወጥ እርድ በወንዞች አካባቢ፣ በሆቴሎች ጀርባና በተለያዩ ቆሻሻ ቦታዎች እንዲሁም ከከተማዋ ውጭ ስለሚከናወን ጥብቅ ቅንጅታዊ ሥራ ይፈልጋል ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ ከእንስሳት ወደ ሰው ተላላፊ ለሆኑ በሽታዎች ከማጋለጥ በተጨመሪ ሥጋው ስለሚመረዝ የጤና ስጋትነቱ በእጅጉ የከፋ መሆኑን ገልፀዋል።
በውይይቱ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ በሚያከናውኑ አካላት ላይ ህጋዊ የገንዘብ ቅጣት እንዲሁም የተፈጠረው ህገ-ወጥነት የከፋ ሆኖ ሲገኝ የእስር ቅጣት እንደሚያስከትል ተገልጿል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ በየትኛውም ቦታ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድን ሲመለከት ጥቆማ በመስጠት መተባበር ያለበት መሆኑ ተነስቷል።
ም/ኮሚሽየር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ከሥጋ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ስታንዳርድ ማስጠበቅ እና ከእርድ ቦታ የማስተካከል ሥራ ጋር በተያያዘም ኮሚሽኑ ቀድሞ ሰፊ ስራ መስራቱንና ለሚመለከታቸው አካላትም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መስራቱን ተናግረዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር እጅግ አደገኛ ህገ-ወጥ ተግባር ከመሆኑም በላይ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ የጤና ችግር ተጋላጭ ስለሚያደርግ ሁላችንም በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መስራት አለብን ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments