የከተማ ግብርና ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ መቅረብ አለበት። አቶ ባዮ ሽጉጤ
የከተማ ግብርና ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ መቅረብ አለበት። አቶ ባዮ ሽጉጤ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም
መጭውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከግብርና ምርት አቅርቦትና ዋጋ ጋር በተያያዘ ተናቦ ለመስራት አርሶ አደርና ከተማ ግብር ልማት ኮሚሽን እና ንግድ ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን መዋቅራቸውን ይዘው የጋራ ስምሪት ወስደዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በማዕከል ሁለት፣ በክፍለ ከተማ 15፣ በወረዳ ደረጃ 53 የባዛር ዝግጅቶች እና በወረዳ ደረጃ 170 የሰንበት ገበያዎች ላይ የከተማ ግብርና ምርት የሚቀርብ መሆኑን ገልፀዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ አያይዘውም ከንግድ ቢሮ እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት ህገወጥነት መከላከልና ሸማቹ ማህበረሰብ በቀጥታ ከአምራቹ ጋር እንዲገናኝ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ንግድ ቢሮም በበኩሉ ከኮሚሸኑ ጋር በቅንጅ እንደሚሰራ፣ የምርት አቅርቦትም ሆነ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትጋት እንደሚሰራ ተገልጿል።
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽንም የከተማ ግብርና ምርት ለሸማቹ በቀጥታ እንዲቀርብ ከማድረግ ጎን ለጎን ጥራቱ፣ ጤንነቱና ኃይጅኑ ተጠብቆ እንዲቀርብ ሰፊ ሥራ ይሰራል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments