ጥራት  ያለው  ወተት   ለህብረተሰቡ  ተደራሽ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ጥራት  ያለው  ወተት   ለህብረተሰቡ  ተደራሽ  እንዲሆን   ቅንጅታዊ  አሰራር  ወሳኝ  ሚና  አለው፡፡

ጥራት  ያለው  ወተት   ለህብረተሰቡ  ተደራሽ  እንዲሆን   ቅንጅታዊ  አሰራር  ወሳኝ  ሚና  አለው፡፡


አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም 


የእንስሳት  ሀብት ልማት  ዳይሬክቶሬት   በ2018 በጀት  ዓመት  ከባለድርሻ  አካላት  ጋር  በቅንጅት  የሚከናወኑ  ተግባራት   እቅድ ላይ   ተፈራረሙ፡፡ 

የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መለስ አንሼቦ  በትስስር ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን  አብራርተዋል።

አያይዘውም ህብረተሰቡን በከተማ ግብርና በስፋት በማሳተፍ ለከተማ የሚስማማ የኤክስቴንሽን ስርዓት ሥራ ላይ በማዋል አርሶ አደሮች ከከተማው ዕድገት ጋር አብረው እንዲለሙ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡

ከባለድርሻ አካላት ጋር የተሰሩ ስራዎች  ነባራዊ ሁኔታ ለመዳሰስ፣በአፈፃፀም ሂደት  ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መለየትና መፍትሄ መስጠት፣በቀጣይ ከባደርሻ አካላት ጋር የሚሰሩ ስራዎችን በማቀድ፣ባለድርሻ አካላት ያላቸውን ልምድ እንዲለዋወጡ  ተደርጓል፡፡

 የወተት ምርትን ከፍ ሊያድርጉ የሚችሉ ስራዎችን ለመስራት፣በወተት ልማት ለተሰማሩ ማህበራት  ድጋፍ ለማድረግ ፣በመኖ ምርት  ከተሰማሩ ማህበራትና ተቋማት  ጋር  (FAO, MSA Buisness Group, EVA,SNV,FSRP እና የኢትዮጵያ እንስሳት እርባታ ማህበር የመሳሰሉት  ባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ ለመስራት እቅድ ላይ ተፈራርመው ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments