
ግብርና ከማምረትም በላይ ነው፡፡
ግብርና ከማምረትም በላይ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን መጭውን የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሸማቹ ማህበረሰብ በቀጥታ ከአምራጮች የግብርና ምርቶችን ማግኘት እንዲችል ሰፊ ሥራ እየሰራ ይገኛል፡፡
የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ባደረሰን መረጃ መሰረት በዛሬው ዕለት በክፍለ ከተማው ለሚካሄድ ባዛር ከ45,000 በላይ እንቁላል ማቅረቡን መረጃ አድርሶናል፡፡
ወረዳው ለበዓሉ ከ5,760 በላይ የሥጋ ዶሮ እንዲሁም የደለበ በግ፣ የደለበ ሰንጋ፣ ቅቤ፣ አይብና ሌሎች የግብርና ምርቶችን ለሸማቹ እንደሚያቀርብ አቶ አንድነት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ገልፀውልናል፡፡
በቀጣይ የጳጉሜ ቀናት ውስጥ ከ170 በላይ በሆኑ የሰንበት ገበያዎች፣ ከ53 በላይ በሆኑ በወረዳ ደረጃ ባሉ ባዛሮች፣ ከ15 በላይ በሆኑ በክፍለ ከተሞች ላይ በተዘጋጁ ባዛሮች እና በማዕከል ደረጃ ባሉ ሁለት ባዛሮች ላይ የከተማ ግብርና በዓይነትና በመጠን ለሸማቹ ማህበረሰብ በአምራቾች በቀጥታ የሚቀርብ መሆኑን ኮሚሽኑ ያስቀመጠው መረጃ ያሳያል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments