
እንቁላል በሁሉም ለሁሉም!፡፡
እንቁላል በሁሉም ለሁሉም!፡፡
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 01 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የከተማ ግብርና ምርት እጥረት እንዳይከሰት በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡
አርቢዎችን በመደገፍ እና የግሉን ማህበረሰብም በማበረታታት የግብርና ምርት በበቂ ሁኔታ ለተጠቃሚው በሰንበት ገበያዎች እና በባዛር ገበያዎች እየቀረበ ይገኛል፡፡
የኮሚሽኑ ተጠሪ ተቋም የሆነው የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከልም መጭውን የአዲስ ዓመት በዓል በተመለከተ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የእንቁላል ምርት እና የደለበ ሰንጋ አዘጋጅቶ ለገበያ እያቀረበ ይገኛል፡፡
በከተማችን አዲስ አበባ ከተማ ግብርና ላይ በተሰራው ሰፊ የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ሥራ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆነው ተሳታፊና ተጠቃሚ ደግሞ የራሱን የቤተሰብ ፍጆታ በመሸፈን ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
በቤተሰብ ፍጆታ ተሳታፊና ተጠቃሚ የሆኑት የግብርና ቤተሰቦች ከራስ ፍጆታ አልፈው ምርታቸውን ለገበያ እያቀረቡ ያሉ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ነው፡፡
ከ2,000 በላይ የሚሆኑ የመንግስት እና የግል ተቋማትም አብዛኞቹ ግብርና ምርት ማዕከል እየሆኑ ያሉ በመሆናቸው የሰራተኞቻቸውን ፍጆታ እየሸፈኑ ይገኛሉ፤ አንዳንዶቹም ከሰራተኞቻቸው ፍጆታ አልፈው ምርታቸውን ለገበያ እስከ ማቅረብ ደርሰዋል፡፡
ከተማ ግብርና ላይ እየታየ ያለው ሰፊ የግብርና ቤተሰብ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ገበያ ላይ ለሚቀርበው የግብርና ምርት መጨመር እና ለዋጋ መረጋጋት ሚናው የማይተካ ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments