
እምርታ!
እምርታ!
እንቁላል በሁሉም ለሁሉም!፡፡
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 03 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የከተማ ግብርና ምርት እጥረት እንዳይከሰት በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ለ11ዱም ክፍለ ከተማ ከ600,000 በላይ የእንቁላል ምርት እያሰራጨ ይገኛል።
ማዕከሉ ሰሞኑን ከፍተኛ የሆነ የእንቁላል ምርት ለተጠቃሚዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች ላይ እያቀረበ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዕንቁላል ምርት አቅርቧል።
የምርት አቅርቦቱ በሁሉም ክፍለ ከተማ ላይ የእንቁላል ዋጋን መተመንም ችሏል። በሁሉም ክፍለ ከተማ ላይ በ12 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
ከተማ ግብርና ላይ እየታየ ያለው ሰፊ የግብርና ቤተሰብ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ገበያ ላይ ለሚቀርበው የግብርና ምርት መጨመር እና ለዋጋ መረጋጋት ሚናው የማይተካ ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments