
“እምርታ ለዘላቂ ከፍታ!”
“እምርታ ለዘላቂ ከፍታ!”
ግብርና ከማምረትም በላይ ነው!፡፡
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
“እምርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በ2017 በጀት በተላየዩ ዘርፎች የተከናውኑ አና የመጡ ለውጦች በከተማ ግብርና በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ላይ በተዘጋጁ የባዛር ቦታዎች እና በሰንበት ገበያዎች ላይ በበቁ ሁኔታ የግብርና ምርቶች ለተጠቃሚዎች ቀርበዋል፡፡
ተጠቃሚዎች በቀጥታ ከአምራቾች የከተማ ግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት በመቻላቸው ደስተኛ እንደሆኑ በባዛርና በሰንበት ገበያ ላይ ያገኘናቸው ገልፀዋል፡፡
የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ለ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከ600,000 በላይ የእንቁላል ምርት ያከፋፈለ ሲሆን ዋጋውም በ12.50 (አሥራ ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) ሲሸጥ ውሏል፡፡
በየክፍለ ከተማው ተዘዋውረን ምልከታ ያደረግን ሲሆን ከእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ውጭ ያሉ ማህበራትም በ14 ብር እና በ14.50 ሲሸጡ መመልከት ችለናል፡፡
አብዛኛው ቦታዎች ላይ በነበረን ምልከታ የእንቁላል ምርት እጥረት አለመኖሩንም ተመልክተናል፡፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ላይ ያሉ ባዛሮችና የሰንበት ገበያዎች ለመጭው አዲስ ዓመት እያቀረቡ ያለው የግብርና ምርት አቅርቦት ሰሞኑንም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments