
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ለሰራተኞቹ ማእድ አጋራ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ለሰራተኞቹ ማእድ አጋራ፡፡
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 05 ቀን 2017 ዓ.ም
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ማዕድ ማጋራት መደጋገፍን፣ አንድነትንና መተሳሰብን የሚያጎላ መልካም እሴት ነው ብለዋል፡፡አያይዘውም ዳግም አድዋ የተደገመበት ዘመን ትውልድ አካል በመሆናችን የዘንድሮውን ዓዲስ ዓመት ስናከብር ድላችን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡
አቶ ጌታሁን አበበ የአስተዳደር ጽ/ቤት ኋላፊ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ 93 ሰራተኞች የዘይትና ዱቄት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ብለዋል፡፡አያይዘውም በዓልን ምክንያት በማድረግ እየተከናወነ ያለው የማእድ ማጋራት መርሀግብር ባህል እየሆነ እንደመጣ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ማእድ ማጋራት የተደረገላቸው ሰራተኞች ካለው ፈታኝ የኑሮ ውድነት የተነሳ ስለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸው አቅርበዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments