
ታላቁ የኢትዮጲያ ሕዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት ሕያው ታሪካችን ነው።
ታላቁ የኢትዮጲያ ሕዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት ሕያው ታሪካችን ነው።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም
"የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት ነው፤ በህብረት ችለናል!!” በሚል መሪ ቃል የኮሚሽኑ አመራሮች እና ሰራተኞች ፓናል ውይይት አካሂዷል።
የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ህዳሴ ግድባችን የመላው ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት ሕያው ታሪክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም በታላቁ የኢትዮጲያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የከተማ አስተዳደሩ መንግስት ሰራተኞች ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ተናግረዋል፡፡
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሀገራዊ መነቃቃት በመፍጠር፣ የይቻላል አስተሳሰብን በማሳየት፣ ለቀጣይ ልማት መሰረት በመሆን ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም ዋና ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
ተወያዮች በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጲያ ሕዳሴ ግድብ መላው ኢትዮጵያውያን ገንዘባችንን፣ ላባችንን እና ደማችንን ያፈሰስንበት በመሆኑ የጋራ ታሪካችን ነው ብለዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በራሳችን አቅም መገንባታችን ኢትዮጵያ እንደምትችል ማሳያ እና የአንድነታችን መገለጫ እንደሆነ የኮሚሽኑ አመራር እና ሰራተኞች ተናግረዋል፡፡
አክለውም እኛ የመንግስት ሰራተኞች ለዚህ የኢትዮጵያውያን ኩራት ለሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የራሳችንን አስተዋጽኦ ማበርከት በመቻላችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ታላቁን የኢትዮጲያ ሕዳሴ ግድብ በተባበረ ክንድ በጋራ ማጠናቀቅ እንደቻልን ሁሉ በቀጣይም መንግስት የሚሰጠንን ተልዕኮ በመቀበል አቅማችን በሚፈቅደው ሁሉ የልማቱ አካል መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments