ማቀድ ብቻ ግብ አይደለም (ባዩ ሽጉጤ ዋ/ኮሚሽነ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ማቀድ ብቻ ግብ አይደለም (ባዩ ሽጉጤ ዋ/ኮሚሽነር)

ማቀድ ብቻ ግብ አይደለም (ባዩ ሽጉጤ ዋ/ኮሚሽነር)


አዲስ አበባ፤ መስከረም 06 ቀን 2018 ዓ.ም


የኮሚሽኑ ጀኔራል ካውንስል አባላት  የሁለት ወር  ስራ አፈጻጸም  ገመገሙ፡፡

የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ልማት ኮሚሺን ዋና ኮሚሽነር  አቶ ባዪ ሽጉጤ  የዝግጅት  ምዕራፍ ላይ አፈጻጸማችን  መገምገማችን  ደህንነቱ  ያልተጠበቀ  የስጋ  እርድና  ዝውውር  ህብረተሰቡ ጋር  ደርሶ  ችግር  ከማድረሱ በፊትና ሌሎች መሰል ጉዳዮች  ለመከላከል   ወሳኝ ጊዜ  እንደሆነ  አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም እቅድን ማቀድ ብቻ ግብ ሳይሆን  በተቀመጠለት የድርጊት መርሀ-ግብር መሰረት ወደ ተግባር ሲቀየር ብቻ ነው  ብለዋል፡፡

 በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሰርተፊኬሽ፣ ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) በዝግጅት  ምእራፍ   ላይ ሆነን  ይኼን ግምገማ  ማድረጋችን የሚበረታታነው  ካሉ  በኋላ  ራሱን ችሎ  የተቋቋመ መ/ቤት  እስካለ  ድረስ  የቤት ለቤት ቅርጫን  አናበረታታም ለማህበረሰቡ  ግንዛቤ መፍጠር ስራ በሰፊው እንሰራለን  ብለዋል፡፡

በመጨረሻም  የካውንስል አባላቱ   በማንዋል እየተከፈሉ ሉ የአገልግሎት ክፍያዎች ው ድጅታል ሲስተም ቢቀየር እና ሌሎች መሰል ሀሳቦች አንስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments