ሙስና   የሚከሰተው  የግለኝነት  አስተሳሰብ  ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ሙስና   የሚከሰተው  የግለኝነት  አስተሳሰብ  ሲነግስ  ነው፡፡

ሙስና   የሚከሰተው  የግለኝነት  አስተሳሰብ  ሲነግስ  ነው፡፡        


 አዲስ አበባ፤ መስከረም 08 ቀን 2018 ዓ.ም


በስነ-ምግባርና ጸረ- ሙስና  መከታተያ  ዳይሬክቶሬት  በአስቸኳይ  ሙስና  መከላከል ላይ ለባለድርሻ አካላት ( ለአርሶ አደሮች እና ልጆች) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መለስ አንሼቦ  ሥነ-ምግባር ማለት ትክክለና አካሄድ ኖሮት የሰውን ነገር ባልተገባ መንገድ መውሰድ የማይፈልግ  የአኗኗር መስመርን የሚከተል ማለት ነው ካሉ በኋላ  ብልሹ አሰራር ላሰብነው የብልጽግና መንገድ እንቅፋት  እንደሆነ በመግቢያ ንግግራቸው  አብራርተዋል፡፡

በመስኩ  ጥናትና  ምርምር ያካሄዱ ምሁራን፣ ዓለም  አቀፋዊ  እና አህጉራዊ  ድርጅቶች  የተለያዩ  መገለጫዎችን መሠረት በማድረግ  ሙስና  ለሚለው ቃል የሰጧቸው  ትርጉሞች  በአገላለጽ የተለያዩ ቢሆኑም በይዘታቸው ግን ተቀራራቢ  እንደሆኑ  ሰነዱን ያቀረቡት የስነ-ምግባርና ጸረ- ሙስና  መከታተያ  ዳይሬክቶሬት  መርጋ ጢጣ ገልጸዋል፡፡
 በመሆኑም ሙስና አደራን አለመጠበቅ፣ እምነትን ማጉደል ወይም አለመታመን፣በጉቦ፣ በምልጃና በአድሎ ሃቅን፣ ውሳኔን ወይም ፍትህን ማዛባት፤ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሲባል ሥርዓቶችን፣ ህጎችን፣ ደንቦችን፣አሰራሮችን፣ መርሆዎችን የመጣስ  ማንኛውም ተግባር እንደሆነ ዳይሬክተሩ አያይዘው አንስተዋል፡፡ 
በመጨረሻም  ተሳታፊዎቹ ላነሷቸው ጥያቄና አስተያት  ምላሽ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments