
በዓላቶቹ እሴታቸውንና ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲያከብሩ ማድረግ ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ነው፡፡
በዓላቶቹ እሴታቸውንና ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲያከብሩ ማድረግ ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ መስከረም 09 ቀን 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን "በእመርታና ማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር" በሚል መሪቃል የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ በተዘጋጀ ሰነድ ከጠቅላላ ሰራተኖች ጋር ውይት ተደረገ፡፡
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሰርተፊኬሽ፣ ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መኖሪያ፣የብዝሀ ሀይማኖቶች ማህደር የአብሮነት እና መቻቻል አብነት እና ብልጽግናን እውን ለማድረግ የምትታትር የብዝሀ ጸጋ ምድር ናት እሚለውን በሰነዱ ላይ አቅርበዋል፡፡
አያይዘውም አብዛኞቹ የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ዘመን መለወጫ በዓላቸውን ወይም የዓመቱን ታላቅ ምስጋና ቀናቸውን የሚያከብሩት በዚሁ በመስከረም ወቅት መሆኑ የነበረ እንጅ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደውሀ ፈሳሽ አይደለም ብለዋል፡፡
የዘንድሮውን መስቀል እና ኢሬቻ በዓላትን ስናከብር ከአባቶቻችን የወረስነውን ጀግንነት ሉአላዊነት ከሀገር ውጭና ውስጥ ባንዳ ማስጠበቅና የዚህን ትውልድ ዳግም አድዋ ድል የሆነውን አባይን መጠበቅ እንዳለብን ም/ኮሩ አክለው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊዎቹ ለተነሱት ጥያቄና አስተያየቶች ምላሽ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments