ኤግዚብሽንና ባዛሮች የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ኤግዚብሽንና ባዛሮች የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አኳያ የላቀ ሚና ይጫወታሉ፡፡

ኤግዚብሽንና ባዛሮች የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አኳያ የላቀ ሚና ይጫወታሉ፡፡


አዲስ አበባ፤ መስከረም  ቀን 14/ 2018 ዓ.ም


"በእምርታ  እና  ማንሰራራት  ለህዝባዊ  በዓላት" በሚል  መሪ ቃል  የመስቀልና  የኢሬቻ  በዓላትን  ምክንያት በማድረግ   ባዛር  ተከፈተ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመስቀልና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚቀርቡበት ደማቅ ባዛር  የተከፈተ ሲሆን ።ኤግዚብሽንና ባዛሮች የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አኳያ የላቀ ሚና እንደሚጫወቱ  ይነገራል፡፡

በባዛሩ የተለያዩ የሰብል ፣ የአትክልትና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋት ፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ  ለሸማች ቀርበው ግብይቱ እየተካሄደ ነው፡፡ይህም በዓላትን ምክንያት በማድረግ ያለ አግባብ የሚፈጠር የዋጋ ጭማሪንና የምርት አቅርቦት  እጥረትን  የሚከላከል  ነው፡፡

በኤግዚቢሽንና ባዛሩ አምራቹና ሸማቹን የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር በቀል ምርቶችን የሚያገኙበት በመሆኑ ነዋሪዎቹ  የህዝባዊ  የበዓላት ዝግጀት የሚሆኑ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ በሚቀርበው አካባቢ በመሄድ ምርቶቹን እንዲሸምቱ  ተጠቁሟል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments