ህገ-ወጥነትን መከላከል የጋራ ተግባራችን መሆን...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

ህገ-ወጥነትን መከላከል የጋራ ተግባራችን መሆን አለበት፡፡ ፀጋ ለማ (ደ/ር)

ህገ-ወጥነትን መከላከል የጋራ ተግባራችን መሆን አለበት፡፡ ፀጋ ለማ (ደ/ር)


አዲስ አበባ፣ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም


በማዕከል ደረጃ የተቋቋመው የህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ቁጥጥር ግብረ-ኃይል በክፍለ ከተማ ደረጃ ለተቋቋመው ተመሳሳይ ግብረ-ኃይል ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ግምገማ አደረገ። 

በማዕከል ደረጃ ከአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፣ ከንግድ ቢሮ፣ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተውጣጣ  የህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር እንዲሁም የቁም እንስሳት ዝውውር ቁጥጥር ግብረ-ኃይል በክፍለ ከተማ ደረጃ ለተቋቋመው ተመሳሳይ ግብረ-ኃይል በህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ፣ ሥጋ እና የቁም እንስሳት ዝውውር ዙሪያ ባለፉት ቀናት ሲሰጥ የነበረውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ግምገመ ተደርጓል። 

የግብረ-ኃይሉ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ኳረንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር እንዲሁም የቁም እንስሳት ዝውውርን በዘላቂነት መቆጣጠር የሚቻለው እስከ ወረዳ ድረስ ላለው ተቆጣጣሪ ተቋማትና አካላት በጋራ በቅንጅት ሲሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራው እስከ ወረዳ ድረስ ላሉ መዋቅሮች እና ለህብረተሰቡ ጭምር የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል። 

ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውር ህብረተሰቡን ለጤና ችግር ሊዳርግ የሚችል፣ ፍትኃዊ ያልሆነ የንግድ ውድድር የሚፈጥር፣ እንደ ቆዳና ሌጦ ያሉ ተረፈ-ምርቶች ባግባቡ ተይዘው ለኢንዱስትሪ ግብዓት እንዳይውሉና እንዲባክኑ የሚያደርግ፣ ለአካባቢ ብክለት መንስዔ የሚሆን በመሆኑ ሁሉም በጋራ ሊታገለው የሚገባ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አክለውም የተጀመረው የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments