
ዜጎች የነቃ ፓለቲካዊ ተሳትፎ በማድረግ ሀገራዊ ዓላማና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ እንደሚችሉ ተገለፀ!!
ዜጎች የነቃ ፓለቲካዊ ተሳትፎ በማድረግ ሀገራዊ ዓላማና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ እንደሚችሉ ተገለፀ!!
የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና" በሚል ርዕስ ለኮሚሽኑ ሰራተኞች የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
በተግዳሮቶች ሳይበገሩ ሀገራዊ ህልወናን ከማስጠበቅ ባሻገር ጂኦ ስትራቴጂያዊ የበላይነት ለማረጋገጥ ከአለም ሀገራት ጋር ፓለቲካዊ ተሳትፎን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ባቀረቡት ሰነድ ላይ ገልፀዋል።
አክለውም ከስትራቴጅካዊ ኩስምና ለመውጣት ሁሉም ዜጋ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በንቃተና በቁጭት መሳተፍ ይገባዋል ብለዋል።
ሌላው የጠላት ውጊያ አቅምን በመስበር የዘመናት ቁጭትን ለመወጣት እና ሀገራዊ እድገት ለማሻሻል እንዲሁም ወደ ከፍታ ለመወጣት በትጋት መስራት እንደሚገባ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
የኮሚሽኑ ሰራተኞችም የቀረበው ሰነድ የያዘው ሃሳብ ትክክልና ገዢ፣ ወቅቱን የጠበቀ፣ ሁሉንም ኢትዮጲያዊ የሚመለከት በመሆኑ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments