
በሦስት ቀናት ውስጥ 330 ሺህ ያክል እንቁላል ለአካባቢው ማህበረሰብ ተሰራጨ።
በሦስት ቀናት ውስጥ 330 ሺህ ያክል እንቁላል ለአካባቢው ማህበረሰብ ተሰራጨ።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም
በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ በማዕከሉ ባሉት የእንቁላል መሸጫ ሱቆች 330 ሺህ ያክል የእንቁላል ምርት ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ተሰራጭቷል።
በማዕከሉ የግብይት ልማት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሣራ ንጉሴ እንደገለፁት በየቀኑ በማዕከሉ ባሉት አስራ አንድ የእንቁላል መሸጫ ሱቆች በአስራ አንድ አምራች ማህበራት የተመረተ እንቁላል ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የተሠራጨ ሲሆን ህብረተሰቡ በፍትሃዊነት እንዲጠቀም የግብይት ስርዓቱን ለመቆጣጠር ማዕከሉ ጠንክሮ መስራት መቀጠሉን አንስተዋል።
መረጃው፡- የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments