አመራርነት በመሪዎች እና በተመሪዎች መካከል ባለ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

አመራርነት በመሪዎች እና በተመሪዎች መካከል ባለዉ ግንኙነት ላይ ትኩረት አድርጎ ይመሰረታል፡፡

አመራርነት በመሪዎች እና በተመሪዎች መካከል ባለዉ ግንኙነት ላይ ትኩረት አድርጎ ይመሰረታል፡፡ 


 አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም


ስነ-ምግባራዊ አመራርነት በመሪዎች እና በተመሪዎች መካከል ባለዉ ግንኙነት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚመሰረት ይነገራል፡፡በመሆኑም  መሪነት ከኋላ ሆኖ ሰዎችን መግፋት ወይም ከፊት ሆኖ መጎተት  ሳይሆን  ሰዎችን ለጋራ ዓላማ እና ግብ በማነቃቃት እና በጎ ተጽዕኖ በማሳረፍ በፍቃደኝነት እንዲያሳኩ ማድረግ የመቻል ጥበብ ነዉ  ያሉት  ሰነዱን ያቀረቡት አቶ አረጋ ፉፋ  ናቸው፡፡

አዎንታዊ ግንኙነት መፍጠር፤የተቋሙን የሥነ-ምግባር መስፈርት ከፍ አድርጎ መቅረጽ፤ተገቢ የሆነ መስተጋብር/ የመግባቢያ እና የትብብር መንገድ መዘርጋት፤ሥነ-ምግባራዊ አጣብቂኞችን መለየት የሥነ-ምግባራዊ አመራር ክህሎቶች  አንሆኑ ተብራርቷል፡፡
 
በመጨረሻም በአራሮቹ ማጠቃለያ ተሰጥቶበት የወርቃማዋ ሰኞ ውይይት ተጠናቋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments