ተቋማዊ ሪፎርም ማከናወን የአገልግሎት አሰጣጡን...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ተቋማዊ ሪፎርም ማከናወን የአገልግሎት አሰጣጡን ያሳልጣል፡፡

ተቋማዊ ሪፎርም ማከናወን የአገልግሎት አሰጣጡን ያሳልጣል፡፡


አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም


የኮሚሽኑ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለጀነራል ካውንስሉ አባላት ቀርቦ ተገመገመ፡፡

ኮሚሽኑ በዝግጅት ምዕራፍ ተቋማዊ ሪፎርም በማከናወን የአገልግሎት አሰጣጡን በማሳለጥ የተጀመረውን ለውጥ በላቀ ደረጀ በማስቀጠል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ አበረታች ተግባራት  መከናወናቸው በሰነዱ ተነስቷል፡፡ 

ከተቋም ግንባታ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ከማሳደግ አንፃር፡የወርቃማ ሰኞ መድረክ ሳይቆራረጥ በመቀጠሉ የሠራተኛዉን ግንዛቤ እዉቀት ማጠናከር ተችሏል፤የኮሚሽኑ ሰራተኞች ነፃ የምሳ አገልግሎት ማስቀጠል መቻሉ፤የተገልጋዮች ምቹ የማረፊያ ቦታ በየኮሪደር በማዘጋጀት እና የተገልጋይ ቀን ሳይቆራረጥ መቀጠሉ፤ከተቋም ግንባታ አንጻር ከማዕከል እስከወረዳ የሰራተኛ ምጥጥን ስራው  ማከናወን መቻሉ፣የሚሰጡ 7 ዋና ዋና አገልገሎቶች ሁሉም በስታንዳርድ መሰጠጡ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር እንደሆነ  የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ተናግረዋል፡፡

የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ስራ ማስቀጠል፤ተዓማኒ የሆኑ መረጃዎችን  በጥራት አደራጅቶ ከማቅረብ አንፃር ውስንነቶች መኖር፤በከተማ ግብርና ስራ ላይ የተሰማሩትን ወደ ስታንዳርድና ጥራት ማምጣት ላይ፤አብዛኞቹ ካፒታል ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ማስገባት ጋር  የተያያዙ እና መሰል ሀሳቦች በውይይቱ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments