ቅንጅታዊ አሰራር ለላቀ ውጤት ወሳኝነት አለው፡፡

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ቅንጅታዊ አሰራር ለላቀ ውጤት ወሳኝነት አለው፡፡

ቅንጅታዊ አሰራር ለላቀ ውጤት ወሳኝነት አለው፡፡   


  አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም


አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን   የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት  ሪፖርት ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር ገመገመ፡፡

በልማት ምክንያት ከይዞታቸው  በልማት ምክንያት ተፈናቀሉአርሶ አደሮች  እና ቤተሰቦቻቸው ማቋቋም፣ከተማ ግብርናን ልማትን  በማስፋፋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ  እና ግብርና ምርትና ግብአት ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ አሰራርን በማሳደግ ህብረተሰቡን የበሽታ  ተጋላጭነት መቀነስና እና አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ በዋናነት  ኮሚሽኑ ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር  በቅንጅት ሊፈጽማቸው የሚገቡ  ዋና ዋና ተግባራት  እንደሆኑ   የሬጉላቶሪ ዘርፍ  ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር)  ባቀረቡት  ሰነድ ላይ  ገልፀዋል። 

የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት  ሪፖርት በቅንጅት የተሰሩ የዝግጅት ምእራፍ ተግባራትን እቅድ አፈጻጸም ለመገምገምና የነበሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች ያመጡትን ውጤቶች ለማሳየት  ይረዳ ዘንድ ውይይቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገንቷል (የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ)

በእቅድ ላይ ውይይት  ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱ ፣ተግባራት በእቅድ መምራት መቻሉ እና ተናባቢ እርምጃ  አወሳሰድና መረጃ አሰጣጥ መጎልበቱ በቅንጅታዊ አሰራር የታዩ ጠንካራ ጎኖች  እንደሆኑ ተብራርቷል፡፡

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች  ለተነሱ ሀሳብና አስተያየት ምላሽ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments