የተሻለ መረጃ   አያያዝ  ተማኝነትን ከፍ ያደር...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የተሻለ መረጃ   አያያዝ  ተማኝነትን ከፍ ያደርጋል።

የተሻለ መረጃ   አያያዝ  ተማኝነትን ከፍ ያደርጋል። 


አዲስ አበባ፣ቀን 6/2/2018 ዓ.ም 


የአርሶ አደርና ከተማ  ግብርና ልማት ኮሚሽን  የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከጠቅላላ ሰራተኞች ጋር ያደረገ ሲሆን  የሪፓርት ግምገማው  ለቀጣይ ቀሪ ወራቶች  ጥንካሬ  መሰረት  እንደሚጥል  ተብራርቷል።


ተቋሙ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት  አኳያ ለስራችን  እገዛ ሊያደርጉ የሚችሉ  የተመረጡ   ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት ስምምነት  ተፈርሞ ወደ ስራ ተገብቷል  ተብሏል የሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ  ፀጋ ለማ ዶ/ር።  

ከዚህ ቀደም በነበሩን የስራ እንቅስቃሴዎች  ስራዎችን በመረጃ አስደግፎ ከመያዝ አንፃር የነበሩብንን  ክፍተቶች  አስተካክለን መቀጠል አለብን ፀጋ  ለማ  ዶ/ር  ) ።
በየደረጃው ያሉ አመራሮች  እና ባለሙያዎች  ተግባራትን ተዋህዶ መፈፀም፣ስራን በየደረጃው እየገመገሙ መሄድ፣ለዝግጅት ምዕራፍ  ጊዜ ሳናባክን የ90 ቀናት እቅድ አውጥቶ  መተግበር መቻሉ  ጠንካራ ጎኖች እንደነሩ  ሰነዱን ያቀረቡት  የእቅድና በጀት  ዝግጅት፣ክትትልና ግምገማ  ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር   በላይነህ ቢሻው  ገልፀዋል። 

የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ  ስራዎችን ማስቀጠል ፤የክትትልና ድጋፍ  ስራዎችን አጠናክሮ  ማስቀጠል፤የካፒታል ፕሮጀክቶችን  ወደ ስራ ማስገባትና በቅንጅት የሚሰሩ ተግባራት  አሰራርን አጠናክሮ መቀጠል  የመሳሰሉት  የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎቻችን ናቸዉ(አቶ ጌታሁን  አበበ  ጽ/ቤት ኃላፊ)።  

በመጨረሻም  ከተሳታፊዎቹ ለተነሱ  ሀሳብና አስተያየቶች  ምላሽ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments