ውስጣዊ ጥንካሬ የሚመጣው ከውስጥ ነው፡፡
ውስጣዊ ጥንካሬ የሚመጣው ከውስጥ ነው፡፡
አዲስ አበባ፣ቀን 10/2/2018 ዓ.ም
እንደ ንስር አሞራ ሕይወትን መቀየር በሚል ርእስ ተፈጥሮ ባስቀመጠችለት መንገድ እንዴት እራሱን እንደሚለውጥና አዲስ ሕይወትን እንደሚጀምር የሚሳይ የንስር ታሪክ በወርቃማዋ ሰኞ መማማሪያ መድረክ ላይ ቀርቧል፡፡
ህይወት ቀጣይነት ያለው የእድገት እና የለውጥ ጉዞ ነው። አንዳንድ ጊዜ፣ እንደገና መጀመር፣ ያለፈውን ትተን አዲስ ጅምር መቀበል እንደሚያስፈልገን ሊሰማን ይችላል ይላል ጥናቱ።ይህ የዳግም ልደት ሂደት እንደገና መጀመር ብቻ ሳይሆን እውነተኛውን ማንነታችንን ገልጦ ከሱ ጋር ተስማምቶ መኖር እንደሆነና ይህን የለውጥ ጉዞ እንዴት መጀመር እና ታላቅ ማንነትን እንደገና መውለድ እንደሚቻል የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አረጋ ፉፋ ባቀረቡት ሰነድ ላይ አመላክተዋል፡፡
ስለሆነም ይላሉ ለውጥ የማይቀር ነው፣ እናም ይህን እውነት በመቀበል፣ እራሳችንን ለአዳዲስ መልካም አጋጣሚዎች እና እድሎች እንከፍታለን። የተለመደውን እና ምቹ የሆነውን ነገር መተው ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የምር የምናድገው እና የምንለወጠው በእነዚያ የለውጥ ጊዜያት ነው።ለውጥን ስንቀበል ካለፈው ውሱንነት ተላቀን ማለቂያ ወደ ሌለው እምቅ አለም እንገባለን ካሉ በኋላ የጽሁፉ አላማ ታሪኩን ወደራሳችን ወስደን እንድንማርበት ነው ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments