የጥሩ ውጤት ባለቤት ለመሆን ጠንካራ የስራ ባህል መገንባት ወሳኝ ነው፡፡
የጥሩ ውጤት ባለቤት ለመሆን ጠንካራ የስራ ባህል መገንባት ወሳኝ ነው፡፡
አዲስ አበባ፣ቀን 10/2/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክርቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል አደረጉ፡፡
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው እና ጠቅላላ ካውንስል አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ተግባቦት ፈጥረን በፍጥነት ወደ ስራ ገብተናል ብለው አያይዘው ገልጸዋል፡፡
የአ/አ/ም/ት/ን/ቱ/ቋ /ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋትዌች ውር የውይይ ብቻ ሳይሆን ግምገማዊ መድረክ ስለሆነ የበለጠ በግልጽነት ለመነጋገር እድል ይፈጥራል ካሉ በኋላ በ1ኛ ሩብ ዓመት የታዩ ጥንካሬዎችን አስቀጥሎ የነበሩ ክፍተቶችን አስተካክሎ ለበለጠ ስራ መነሳሳትን መፍጠር ትኩረት ሰጥቶ መስራት አስፈላጊ ነው፡፡
አጋረደች ጀማነህ (ዶ/ር) የአ/አ/ም/ት/ን/ቱ/ቋ /ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ በጋራና በተደራጀ መንፈስ ሰርታችሁ የጥሩ ውጤት ባለቤት እንድትሆኑ ጠንካራ የስራ ባህል መገንባት አለባችሁ ካሉ በኋላ የጎዳና ውሾች ጉዳይ በትኩረት እንዲሰራበት በማለት አስምረው አልፈዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments