የከተማ ግብርና ምርታማነት የነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ያረጋግጣል።
የከተማ ግብርና ምርታማነት የነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ያረጋግጣል።
አዲስ አበባ፣ቀን 11/2/208 ዓ.ም
ከማእከል ዳይሬክተሮች ፣ቡድን መሪዎች እና ከክፍለከተማና ወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ሪፓርት እና የ4ኛ ዓመት 1ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ አፈፃፀም ተገመገመ።
የከተማ ግብርና ዘርፍ ከወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተለይም ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ የዋጋ ግሽበት እና የምግብ አቅርቦት እጥረት የገጠሙንን ፈተናዎች ለመሻገር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ በሪፓርቱ ተነስቷል።
ስለሆነም ህ/ሰቡን በከተማ ግብርና በስፋት በማሳተፍ ለከተማ የሚስማማ የኤክስቴንሽን ስርዓት በመዘርጋት ጤናማ የሆነ የግብርና ምርት አቅርቦት ማሳደግ እና የህሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው ተብሏል።
የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮ መለስ አንሸቦ የከተማ ግብርና ባህል እየሆነ መምጣቱና በአነስተኛው ቦታ ብዙ ማምረት የሚያስችሉ ቴክኖሎጅዎች እየተስፋፉ ለመምጣታቸው የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ትልቁን አስተዋፅኦ አበርክቷል ካሉ በኋላ ኮሚሽኑ ጥሩ ውጤት የሚያመጣው ብቻውን ስለሰራ ሳይሆን ከክፍለከተማ እስከወረዳ በተዘረጋው ሰንሰለታችን በጋራ ስለ ሰራን ነው ብለው አያይዘው ገልፀዋል ።
የሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ(ዶ/ር) የከተማ ግብርና ስራዎች ዝም ብለው የሚሰሩ ሳይሆን በስታንዳርዱ መሰረት መሰራታቸውንም እያረጋገጥን ሲሆን የአገልግሎት አሰጣጥና የምርት ጥራት ከሌለ በህብረተሰባችን ላይ ችግር ይደርሳል ብለዋል።አያይዘውም ለስራችን እንቅፋት የሆኑብን ጉዳዮች የመኖ እና የዶሮ ጫጩት በመሆናቸው በትስስር ለመፍታት ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል።
የአርሶ አደር ማቋቋም ልማት ም/ኮ ሎኮ ዳለቻ ለከተማችን ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠርና ፀጋዎቻችን ለይተን በአግባቡ መጠቀም ላይ በትኩረት እየሰራን ነው። እናንተም ተንቀሳቀሱ ኮሚሽኑም ምቹ የስራ ቦታ ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለው አያይዘው ገልፀዋል።
የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ስራዎችን ማስቀጠል ፤የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል፤የካፒታል ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ማስገባትና በቅንጅት የሚሰሩ ተግባራት አሰራርን አጠናክሮ መቀጠል የመሳሰሉት የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎቻችን ናቸዉ ተብሏል።
በመጨረሻም በተነሳው ሀሳብና አስተያዬቶች ምላሽ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments