ሙስና ሲቀንስ ምርታማነት ይጨምራል፡፡
ሙስና ሲቀንስ ምርታማነት ይጨምራል፡፡
አዲስ አበባ፣ ቀን 13/2/2018 ዓ.ም
የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙሥና መከታተያ ዳይሬክቶሬት በሥነ-ምግባርና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ከ10 በላይ ለሆኑ አመራሮች እና 120 በላይ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ ።
የአርሶ አደር ማቋቋም ልማት ዘርፍ ም/ኮ ሎኮ ዳለቻ የሥነ-ምግባር እና መልካም አስተዳደር ችግር የሰው ልጅ ወደዚች ምድር ከመጣ በኋላ የሚፈጠርና የሚፈታውም በሰው ልጅ የሆነ ሰው ሰራሽ ባህሪዎች ናቸው ብለው በመክፈቻ ንግግራቸው አስቀምጠዋል።
መልካም አስተዳደር የህዝብ ጥቅምና ፍላጎት የሚገለፅበት፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚረጋገጠበት፣የዜጎች ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚረጋገጥበት፣ለህዝብ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ የሚሰጥበት፣ተጠያቂነትን የሚያሰፍን እና የህግ የበላይነት የሚረጋገጥበት መሆኑን በፀረ- ሙስና እና ስነምግባር ኮሚሽን ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ አቶ ደረጀ ግርማበሰነዱ ላይ አንስተዋል፡፡
የቁርጠኝነት ማነስ፣የአቅምና ብቃት ማነስ፣የቢሮክራሲ ችግሮች፣ሙስናና ብልሹ አሠራር፣ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በስፋት አለማሳተፍ እና ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት የመልካም አስተዳደር ተግዳሮቶች እንደሆኑ አያይዘው ገልፀዋል ፡፡
የሥነ-ምግባር መርሆዎች ለድርጊት መመሪያ በመሆናቸው ስለሆነም እሴቶችን ለመተግበርና የአገልጋዩ ባህሪ ለአገልግሎት አሰጣጡ የሚመጥን እንዲሆን ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ድርጊቱ መርህን ተከትሎ መሰራት አለመሰራቱ ላይ ትኩረት ማድረግ እና የግለሰቦች የስነ-ምግባር ልማት ላይ ትኩረት ማድረግ የሥነ-ምግባር ንድፈ ሃሳቦች መርህ እንደሆኑ ተብራርቷል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments