የሳይበር ደህንነት ሰዎችን እና መረጃዎችን ከሳይበር ጥቃት መጠበቅ ነው፡፡
የሳይበር ደህንነት ሰዎችን እና መረጃዎችን ከሳይበር ጥቃት መጠበቅ ነው፡፡
አዲስ አበባ፣ ቀን 17/2/2018 ዓ.ም
ሳይበር ደህንነት ሲስተምን፣ ኔትወርኮችን እና ፕሮግራሞችን ከዲጂታል ጥቃቶች የመከላከያ ቴክኒክ ነዉ፡፡
የሳይበር ደህንነት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን፣ የዲጀታል መረጃ ሂደቶችን እና ፖሊሲዎችን በመጠቀም ሰዎችን እና መረጃዎችን ከሳይበር ጥቃት የመጠበቅ ስልት ነው፡፡እንዲሁም የሳይበር ደህንነት ግለሰቦች፣ድርጅትን ፣መረጃዎች እና ንብረቶቹን ከሳይበር አደጋዎች መጠበቅ እንደሆነ ተብራርቷል፡፡
በመሆኑም መረጃዎችን እና ኔትወርኮችን ካልተፈቀደ አካል ይከለክላል፣ሚስጥራዊነት ያለው የግል እና የፋይናንሺያል መረጃዎችን ይጠብቃል፣ዲጂታል ሲስተሞችን ከጥቃት ይጠብቃል፣ለሀገር ደህንነት/National security/፣ውድ የሆኑ መስተጓጎሎችን ይከላከላል፣የደንበኞችን እምነት ለማሳደግ ይረዳል (የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ቡድን መሪ አቶ ጌቱ በቀለ በሰነዱ ላይ አንስተዋል)፡፡
እንደ ጠንካራ የይለፍ ቃል ፖሊሲ እና ነባሪ ቅንብሮችን መቀየር ያሉ መሰረታዊ እርምጃዎችን መተግበር የአይቲ ደህንነትን ማረጋገጥ ይቻላል ተብሏል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments