በእንስሳት ልማት እና የእንስሳት ተዋፅኦ ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
በእንስሳት ልማት እና የእንስሳት ተዋፅኦ ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ በሚሊኒየም አዳራሽ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የእንስሳት ልማት እና የእንስሳት ተዋፅዖ አውደ ርዕይ በይፋ ተከፍቷል።
በአውደ ርዕዩ ከ14 ሃገራት የተውጣጡ ከ100 በላይ የዘርፉ ተዋንያን፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉ እንደሆነ ከግብርና ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽንም በአውደ ርዕዩ ላይ በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ ያለውን የከተማ ግብርና እንቅስቃሴና እየተመዘገበ ያለውን ውጠየት የሚገልጽ አስረጅዎችን ይዞ መቅረቡን ተመልክተናል፡፡
ይህ አውደ ርዕይ ከፍተኛ ልምድና ተሞክሮ የሚቀሰምበት መሆኑን በአውደርዕዮ ላይ የተገኙት የኮሚሽኑ አመራሮችና ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡
አውደ ርዕዩ በቀጣይ ቀናትም የሚቀጥል ሲሆን ኮሚሽኑም የግብርና ምርትና አገልግሎቶችን ይዞ በመገኘት ለህዝብ የማስተዋወቁ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments