ግብርና በባህሪው ተከታታይነት ያለው ሙያዊና ቴክኒካል ድጋፍና ክትትል ይፈልጋል፡፡
ግብርና በባህሪው ተከታታይነት ያለው ሙያዊና ቴክኒካል ድጋፍና ክትትል ይፈልጋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥቅምተ 21 ቀን 2018 ዓ.ም
ከኮሚሽን እና ከክፍለ ከተማ የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ላይ በከተማ ግብርና ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የሰነድ እና የመስክ ምልከታ ማድረጋቸውን የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንድነት አሳውቀውናል፡፡
ግብርናን አጠናክሮ ለማስቀጠል በአካል ተገኝቶ ሙያዊና ቴክኒካል ድጋፍ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑንም የጽ/ቤት ኃላፊው አያይዘው ገልፀዋል፡፡
ግብርና ተፈጥሯዊ ባህሪው በመስክ ተገኝቶ ሙያዊና ቴክኒካል ድጋፍና ክትትልን የሚፈልግ ዘርፍ በመሆኑ ተከታታይነት ያለው በግብዓትና ቴክኖሎጂ የተደገፈ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ከዘርፉ ባለሙያዎች የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments