ግብርና ከማምረትም በላይ ነው።

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ግብርና ከማምረትም በላይ ነው።

ግብርና ከማምረትም በላይ ነው።


አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም



ግብርና ንቅናቄ፣ መነቃቃት፣ ክትትል፣ ድጋፍ፣ በአካል እይታ፣ ... የሚፈልግ ዘርፍ መሆኑን በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐመድ ልጋኔ ገልፀዋል።
የኮሚሽኑ አመራሮች፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ የክፍለከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎች እና የሚዲያ አካላት በአርሶ አደር ማቋቋም እና በከተማ ግብርና ዘርፍ በተለይም በሌማት ትሩፋት የተሰሩ ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለጃ ጉብኝቱ ዋነኛ ትኩረቱ የልምድ ልውውጥ በማድረግ አንዱ ጋር ያለውን መልካም ተሞክሮ ወደልላው ማስፋት መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም የልምድ ልውውጥ ማድረጉ በየተራ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ላይ በየተራ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።
በጉብኝቱ ተሳታፊ የነበሩት አመራሮችና ባለሙያዎች በተመለከቱት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን አንስተዋል።
ጉብኝቱ የተደረገባቸው ተጠቃሚዎች ኮሚሽኑ በበቂ ሁኔታ ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን አንስተው ለተደረገላቸው ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኔ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለው አመራርና ባለሙያ መደበኛ ተግባሩ ተጠቃሚዎችን በመስክ ተገኝቶ ሙያዊ እና ቴክኒካል ድጋፍ መስጠት በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments