እጅግ በጣም አመርቂና የተጠናከረ የአርሶ-አደርና...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

እጅግ በጣም አመርቂና የተጠናከረ የአርሶ-አደርና የከተማ ግብርና ልማት ሥራዎች  እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ።

እጅግ በጣም አመርቂና የተጠናከረ የአርሶ-አደርና የከተማ ግብርና ልማት ሥራዎች  እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ። 
-------------------------
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ባደረገው የደስክና የመስክ ምልከታ አበረታች የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ልማት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጿል። 

ቋሚ ኮሚቴው የኮሚሽኑን የሦስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ያዳመጠ ሲሆን፤ ተግባራዊነቱንም ለማረጋገጥ በከተማዋ እየተሰራ ያለውን  የከተማ ግብርና ስራ ተዘዋውሮ ተመልክቷል። 

የቋሚ ኮሚቴው የቡድን አስተባባሪ የተከበሩ ወ/ሮ ተስፋነሽ ተፈራ በሪፖርት የተገለፀው እና በመስክ የተመለከቱት አዲስ አበባ ላይ ከተማ ግብርና በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ያመለክታል ብለዋል።

የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ቋሚ ኮሚቴው በዚህ ልክ በዴስክ እና መስክ ላይ ተገኝቶ ሥራችንን ተመልክቶ ለሰጠን ድጋፍና ግብረ-መልስ ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል።

የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኔ  ከተማ ግብርናን በዘመናዊ መንገድ ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሃብት ለማሰማራት በተለይም ከትራንስፖርት ጋር በተያያዘ ፌደራል መንግስቱ በተለይም ግብርና ሚኒስትር እና ቋሚ ኮሚቴው ሊያግዝ ይገባል ብለዋል።

የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ኮሚሽኑ በርካታ ሰው ተኮር ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን፤ የግብርና ምርት ጤንነትና ደህንነት የማስጠበቅ ተግባርም በኮሚሽኑ እና በቅንጅት ትኩረት በስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ልዑካን ቡድን በቂርቆስ እና አቃቂ ክፍለ ከተሞች ላይ ተዘዋውረው በተመለከቱት የግብርና ሥራ እጅግ በጣም የተደሰቱ መሆኑን ገልፀዋል።

ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ዛሬ ከተማ ግብርና አበረታች ውጤት እያመጣ ለመሆኑ ተጠቃሚዎቻችን ከአንድ ማሊዮን በላይ ደርሷል ብለዋል።

አክለውም ክቡር ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ለከተማ ግብርና በሰጡት ልዮ ትኩረት እና በሌማት ንቅናቄ ፕሮግራም አሁን ላይ ከተማ ግብርና አዲስ አበባ ላይ ባህል እየሆነ መምጣት ችሏል ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments