የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የግብርና ጉዳዮ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የግብርና ሥራዎችን ተዟዙረው ጎበኙ።

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የግብርና ሥራዎችን ተዟዙረው ጎበኙ።

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በቂርቆስ እና አቃቂ ክፍለ ከተሞች ተገኝተው በከተማ ግብርና እና በሌማት ትሩፋት እየተሰሩ የሚገኙ እጅግ በጣም አመርቂ የሆኑ ሞዴል ሥራዎችን ተዟዙረው ተመልክተዋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቤተሰብ ፍጆ ላይ የተሰራ የተቀናጀ ከተማ ግብርና፣ እዚያው ወረዳ 02 የጣራላይ እርሻ፣ ወረዳ 04 አቢዮት ቅርስ ትምህርት ቤት አኳ ፎኒክ (በአፈር አልባ ቴክኖሎጅ) የለማ ዘመናዊ የአትክልት ልማት፣ የወተት ላም ክላስተር፤ በአቃቂ ቃልቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የተቀናጀ የከተማ ግብርና፣ በወረዳ 09 የንብ ክላስተር፣ የዶሮ እሴት ሰንሰለት ክላስተር  እና የጤፍና የአትክልት ክላስተርን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም እጅግ በጣም ደስተኛ እንደነበሩና አዳስ አበባ ላይ እየተሰራ ያለው የከተማ ግብርና ሥራ ሞዴል መሆኑን ገልፀዋል።

የልዑካን ቡድኑ አስተባባሪ ክብርት ወ/ሮ ተስፋነሽ ተፈራ ቋሚ ኮሚቴው ተዘዋውሮ የተመለከታቸው የከተማ ግብርና ሥራዎች በቢሮ ከቀረበላቸው ሪፖርት ጋር ተናባቢ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከሪፖርቱ በላይ እጅግ በጣም ማራኪ የሆነ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በከተማ አስተዳደሩ በከተማ ግብርናና በሌማት ትሩፋት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን መመልከት እና አዲስ አበባ ላይ የከተማ ግብርና አይቻልም የሚለውን አመለካከት በመቀየር የይቻላል አስተሳሰብ የበለፀገ መሆኑን ማሳየት ነው ብለዋል።

የሁለቱም ክፍለ ከተሞች አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች የከተማ ግብርና በከተማ አስተዳደሩ ከቤተሰብ ፍጆታ አልፎ ለብዙዎች የገቢ ምንጭ መሆንና ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑን አንስተዋል።

ሁለቱም ክፍለ ከተሞች ላይ የተገኙ የማዕከል፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎችም ቋሚ ኮሚቴው ተዘዋውሮ የተመለከታቸው የግብርና ሥራዎች እና የተሰጠው አስተያየት ለግብርና ቤተሰብ ትልቅ ግብዓት ናቸው ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments