የከተማ ግብርና አዲስ አበባ ላይ ለዘላቂ ኢኮኖሚ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የከተማ ግብርና አዲስ አበባ ላይ ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

የከተማ ግብርና አዲስ አበባ ላይ ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አዲስ አበባ ላይ የከተማ ግብርና ለኢኮኖሚው ዘርፍ ትልቅ አቅም እየሆነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን እያከናወነ ያለውን ተግባር በዴስክና በመስክ ምልከታ አድርጎ ለኮሚሽኑ ጀነራል ካውንስል ግብረ-መልስ ሰጥተዋል፡፡

የተከበሩ የም/ቤት አባላት በክብርት ወ/ሮ ተስፋነሽ ተፈራ ቡድን መሪነት እየተመራ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት እና ወረዳ አራት እንዲሁም አቃቂ ቃልቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት እና ዘጠኝ ላይ በመዘዋወር የመስክ ምልከታ አካሂዷል።

በመስክ የተመለከቱትንም በሪፖርት አደራጅተው አጥጋቢ ግብረ-መልስ ሰጥተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በወተት ላም እርባታ፣ በዶሮ እርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በማድለብ፣ በግቢና በጓሮ አትክልት እንዲሁም በሰብል ልማት የተከናወኑ ተግባራትን ተዘዋውሮ መመልከቱን ቋሚ ኮሚቴው በሪፖርቱ አመልክቷል።

አያይዘውም ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ፣በጉድለትና ሊተኮርባቸው ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች ለተቋሙ አመራርና ባለሙያዎች በሪፖርቱ አመላክቷል።

የኮሚሽኑ አመራሮች፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና የአቃቂ ቃልቲ ክፍለ ከተማ የዘርፉ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም ቋሚ ኮሚቴው ቢያግዘን ያሉትን ሃሳብ በዝርዝር አስቀምጠዋል። የትራንስፖርት እጥረት፣ ኮሚሽኑ ወደ ቢሮ ከፍ ይበልልን የሚል፣ የእንስሳት መኖ ዋጋ፣ የአርሶ አደሮች መልሶ መቋቋምና መልማት፣ ጤንነቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ የግብርና ምርት ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ ለማድረግ በተለይም ቄራዎችን ከማዘመን ጋር በተያያዘ፣ የግብዓትና ቴክኖሎጅ አቅርቦት ችግሮች (እጥረቶች)  እንዲፈቱልን በሚመለከታቸው አካላት እገዛ እንዲደረግልን በእናንተ በኩል ብታግዙን የሚል አስተያየትና ጥያቄ አቅርበዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተለይ ግብርና ሚንስቴር፣ ከተማ ልማት ሚንስቴርና ግብርና ባለስልጣን ተደራጅተው መጥተው ቢጎበኙን ከዚያም በሚጠበቅባቸው ልክ ዕንዲያግዙን በእናንተ በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ቢደረግ ብለዋል።

የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ኮሚሽኑን ወክለው በቋሚ ኮሚቴው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፤ ከተማ ግብርና አዲስ አበባ ላይ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በመስበር እንደሚቻል ያሳየ መሆኑን ገልፀዋል፤ ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ተዘዋውሮ በአርሶ አደር መልሶ ማቋቋምና ልማት፣ በእንስሳት እና እጽዋት ዘርፍ ላይ የተሰሩትን ስራዎች ተመልክቶ አስተማሪ የሆነ ሪፖርትና ግብረ-መልስ በመስጠቱ አመስግነዋል፤ በቀጣይም ድጋፍና ክትትላችሁ አይለየን ሲሉ አጽህኖት በመስጠት ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments