ለ202 ነዋሪዎች 1 ሺ 200 እንቁላል ጣይ ዶሮ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ለ202 ነዋሪዎች 1 ሺ 200 እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ከመኖ ጋር ተበረከተ፡፡

ለ202 ነዋሪዎች 1 ሺ 200 እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ከመኖ ጋር ተበረከተ፡፡

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም 

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ስታንዳርቡን የጠበቀ የብረት ኬጂን ጨምሮ ለ200 ቤተሰብ ፍጆታ፤ ለ2 ፋምሊ ቢዝነስ ባለ 100 ኬጂ 2 እንዲሁም 1,200 ቄብ ዶሮዎች ከ50 ኩንታል መኖ ጋር ለተጠቃሚዎች አበርክቷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሳራ አስራት፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ፣  የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በለጠች ተሰማ፣ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሕይወት ተስፋዬ ተገኝተው ኬጆችን ለነዋሪዎቹ  አስረክበዋል፡፡

የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሳራ አስራት ምግቤን ከደጄ በሚል እንቅስቃሴ የተጀመረው የከተማ ግብርና ስራ ወደ ሌማት ቱሩፋት ከፍ እንዲል በማድረግ ባለፉት አራት ዓመታት እንደ ሀገር፣ እንደ ከተማ ብሎም እንደ ክፍለ ከተማችን ሰፋፊ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ብለዋል፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ ከተማ ግብርና ለርካታ ነዋሪዎች ከቤተሰብ ፍጆታ አልፎ የሥራ ዕድል በመፍጠር ምርታቸውን ወደገበያ በማውጣት ገቢ ማግኘት እንዲችሉ አድርጓል ብለዋል፡፡

ወ/ሮ በለጠች ተሰማ በበኩላቸው የሌማት ቱሩፋት መርሃ-ግብር በክፍለ ከተማው አርእያ በሆኑ እና ታታሪ በሆኑ የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚዎች አማካኝነት የብዙዎችን ሕይወት በመቀየሩ ብዙዎቹ የከተማችን ነዋሪዎች ከሸማችነት ወደ አምራጭነት ተሸጋግረዋል ለዚህም የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ምስክር ናቸው ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments