መሪነት ሌሎች ያላዩትን የማየት ጥበብ ነው፡፡
መሪነት ሌሎች ያላዩትን የማየት ጥበብ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም
ድፍረት፣ልግስና፣ ጥበብ፣የመቋቋም ችሎታ፣ቁርጠኝነት፣መላመድ፣ርህራሄ፣. የማወቅ ጉጉት፣ብሩህ አመለካከት፣የፈጠራ ችሎታ፣. ጥልቅ ስሜት፣ታማኝነትና ድፍረት አንድ ሰው ጥሩ መሪ ለመሆን ሊኖሩት የሚገቡ ባህሪያት ናቸው(አቶ ሲሳይ አንሰኔ)፡፡
የመሪነት ስራ ሰዎች ሲወድቁ ማንሳት ከቆሙም ከፍ ብለው አንዲቆሙ ማድረግ ነው። ይህን ለማድረግ መሪ ያለማቋረጥ አዎንታዊ መሆን አለበት፤ አንድ ሰው የሌለውን ሊሰጥ አይችል፤ ከዘላቂ ተሰፋቸው የተነሳ ትልልቅ አደጋ ሊያመጣ የሚችሉ እርምጆዎችን ይወስዳሉ፣ ሌሎችን አንዲወሰድ ያበረታታሉ የሚሉትን ሀሳቦች በሰነዱ ላይ አንስተዋል፡፡
መሪዎች በገንዘባቸው ፣ በሰአታቸው፣ በእውቀታቸው፣ በችሎታቸው ለጋሶች መሆን አለባቸው፡፡ እንድ ሠው የሚቀበለው ሳይሆን የሚሠጠው ትልቅ ያደርገዋል ፡፤በመሆኑም መሪነት በመሰጠት ጥሩ መሪዎችን ገልብጦ መቀበል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments