ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር በአርሶ አደር አይናለም እየተሰራ ያለውን የአሳ እርባታ እና ቦሌ ወረዳ1 የዶሮ እርባታና ከብት ማድለብ ማእከል ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ እና ምክትል ኮሚሽነር ሙሀመድ ልጋኔ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር በአርሶ አደር አይናለም እየተሰራ ያለውን የአሳ እርባታ እና ቦሌ ወረዳ1 የዶሮ እርባታና ከብት ማድለብ ማእከል ጎበኙ፡፡
ኮሚሽነሩ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ ጋር በመሆን ባደረጉት ጉብኝት የአሣ እርባታው የሥራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም የምግብ ፍጆታን በማሟላት በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ኮሚሽነሩ ገልጸው፣ የወረዳው እና የክፍለ ከተማው አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤ ኃላፊዎችና ድጋፍ ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
በአርሶ አደር አይናለም እየተሰራ ያለው የአሳ እርባታ የስራ እድል ከመፍጠር አልፎ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ መስገኘት መቻሉን ገልጸው ከዚህም በላይ በሰፊው ማልማት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ።
ሌላው የጉብኝቱ አካል የነበረው በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ1 በዶሮ እርባታና ከብት ማድለብ ዘርፍ የተሰማሩ የከተማ ግብርና ሥራው አካል የሆነው ማዕከል ለነዋሪዎቹ የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥና በኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ከማሳደግ አንጻር ቀላል የማይባል ሚና እንደሚጫወቱ ተገለጸ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments