ዓለምን  ወደ  አንድ  መንደር  መቀየርና  ለነ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ዓለምን  ወደ  አንድ  መንደር  መቀየርና  ለነቃ ማህበረሰብ   መፈጠር   የማህበራዊ  ሚዲያ  ትልቅ  ድርሻ  አለው፡፡

ዓለምን  ወደ  አንድ  መንደር  መቀየርና  ለነቃ ማህበረሰብ   መፈጠር   የማህበራዊ  ሚዲያ  ትልቅ  ድርሻ  አለው፡፡

አዲስ አበባ፤ ህዳር 4 ቀን  2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን እንስሳት ልማት ልህቀት ማእከል ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች  በማህበራዊ  ሚዲያ አጠቃቀም፣በቀውስ ጊዜ ኮሙኒኬሽን፣በህዝብ አስተያየት ቅሬታና አቤቱታ አቀባበልና መስተንግዶ  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልተና ተሰጠ፡፡

የስልጠናው  አላማ  መሰረታዊ  የማህበራዊ  ሚዲያ ምንነት፣ ተግዳሮቶች፣ ጥቅሞች እና አጠቃቀም፣ የሥነ-ልቦና ጥቃቶችን መከላከል እንደሆነ  ተነግሯል፡፡

አሳታፊነት፣ክፍትነት፣የጋራ ፍላጎቶችን ማንፀባረቁ፣ድንበር የለሽ እና ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው መሆኑ፣ተለዋዋጭ ባህሪይ፣ማንነትን ደብቆ መንቀሳቀስ የሚያስችል መሆኑ፣ ውስብስብነቱ ፣መዋቅራዊ ስርዓት የለውም፣ኢንተግሬትድ (የብዙ ነገሮች ውህድ) መሆኑ፣እርስ በርስ የተሳሰረ መሆኑ፣ፈጣን እና በርካሽ ዋጋ መገኘቱ የማህበራዊ ሚዲያ ባህሪያቶች እንደሆኑ በሰነዱ ላይ ተመላክተዋል፡፡

ዓለምን ወደ አንድ መንደር መቀየሩ፣ገዥና ሻጭን በቀጥታ ማገናኘቱ፣ለቴክኖሊጂ ሽግግር ማገልገሉ፣የነቃ ማህበረሰብ ለመፍጠር ማስቻሉ፣መረጃ ለማግኘት፣ ለማሰራጨት እና ለማከፋፈል ማስቻሉ፣መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ማስቻሉ፣ጋዜጠኞች የማይደርሱበትን ክስተት ለመዘገብ ማስቻሉ እና በቀላሉ ታዳሚዎችን ማማለል ማስቻሉ የመሳሰሉት የማህበራዊ ሚዲያ ጥቅሞች  እንደሆኑ ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

ለባዕዳን ባህሎች ወረራ ጥቃት ያጋልጣል፣የፖረኖግራፊ ፊልሞችን እና እንቅስቃሴዎችን ያስፋፋል፣አላስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ፣አሉታዊ ግንኙነቶችን፣ የማጭበርበር፣ የሽብር እንቅስቃሴዎችን ያስፋፋል፣ስም የማጥፋት ዘመቻዎችን ያስፋፋል፣ የአገርን በጎ ገፅታ ያጠለሻል፣ለስህተቶች/ክስተቶች ፈጣን የሆነ መጥፎ ግብረመልስ ይፈጥራል፣ማህበራዊ ሚዲያ አብዛኛው በምዕራባዊያን እጅ ስለሆነ ጥገኛ ያደርጋል፣የቅጅ መብቶችን መፃረር እና ከቤተሰብ መነጠል፣ ብቸኝነትን ማስፋፋት የማህበራዊ ሚዲያ አሉታዊ ገፅታዎች ናቸው፡፡

በማህበራዊ  ሚዲያው  ዘርፍ  የበላይነትን  ማረጋገጥ  የሚያስችል   አቅም መፍጠር ከስልጠናው  የሚጠበቅ እንደሆነ ስልጠናውን  የሰጡት  የኮሙኒኬሽን  ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር  ወንደወሰን  አካሌ ገለጹ፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments