በማዕከሉ ውስጥ ላሉ የወተት  እና  የሚደልቡ  ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

በማዕከሉ ውስጥ ላሉ የወተት  እና  የሚደልቡ  ከብቶች ክትባት ተሰጠ።

በማዕከሉ ውስጥ ላሉ የወተት  እና  የሚደልቡ  ከብቶች ክትባት ተሰጠ። 

እ/ል/ል/ማ፤ አዲስ አበባ (ህዳር 04/2018 ዓ.ም)
==== 

በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ለወተት ላሞች፣ ጊደሮች እና ለሚደልቡ የዳልጋ ከብቶች የጎሮርሳ (Bovine pastuerolosis) በሽታ መከላከያ ክትባት ተሰጠ። 

በሽታው በባክቴሪያ የሚመጣና የእንስሳቱን የመተንፈሻ አካላት የሚያጠቃ ሲሆን በድርቅና በተጨናነቀ ሁኔታ የመነሳት አጋጣሚ እንዳለው ባለሙያዎች ይገልፃሉ።
ክትባቱ ከ3 ወር በላይ ለሆኑ ጥጆች እና ለክበድ ላሞች በዓመት ሁለት ጊዜ በመስጠት በሽታውን መከላከል እንደሚቻል የዘርፉ ባለሙያዎች ጨምረው ተናግረዋል። 

በማዕከሉ በሁሉም ክላስተሮች ክትባት የመስጫ መርሃ ግብራቸውን ጠብቀው እየተሰጡ መሆኑ በሽታው ከመከሰቱ በፊት የሚመጣውን ሁለንተናዊ ኪሳራ መከላከል እንዲቻል እንደሚረዳ ይታመናል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments