ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውር ህብረተሰቡን ለጤና ችግር ተጋላጭ ያደርጋል፡፡
ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውር ህብረተሰቡን ለጤና ችግር ተጋላጭ ያደርጋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጋር በመተባበር ህገ -ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውርን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ውይይት አደረገ፡፡
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር አመራሮችና አባላት፣ የሥጋ ማጓጓዣ መኪና ባለንብረቶች ማህበር አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ህገወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ላይ ያተኮረ ሰነዶች ቀርበው ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡
ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውር ህብረተሰቡን ለጤና ችግር ሊዳርግ የሚችል፣ ፍትኃዊ ያልሆነ የንግድ ውድድር የሚፈጥር፣ እንደ ቆዳና ሌጦ ያሉ ተረፈ-ምርቶች ባግባቡ ተይዘው ለኢንዱስትሪ ግብዓት እንዳይውሉና እንዲባክኑ የሚያደርግ፣ ለአካባቢ ብክለት መንስዔ የሚሆን በመሆኑ ሁሉም በጋራ ሊታገለው የሚገባ ተግባር መሆኑን ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
የከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ም/ክ ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር ) የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን እንዲሁም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ በጋራ በመሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል ።
በቀጣይም ቅንጅታዊ ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥልና ጥራቱን፣ደህንነቱና ሀይጅኑ የተጠበቀ ለተጠቃሚው እንዲደርስ በጋራ የሚሰሩ መሆኑን ተቋማቱ የጋራ አድርገዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
Gmail ➲ farmeragr2020@gmail.com
Website ➲ http://aafuadc.gov.et/
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments