የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ለማዘመን የሚያግዝ አሰራር ስርዓት መዘርጋት ወሳኝ ነዉ፡፡
የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ለማዘመን የሚያግዝ አሰራር ስርዓት መዘርጋት ወሳኝ ነዉ፡፡
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ምሰረታ ተካሄደ፡፡
ተገልጋዮች በተሳትፎአቸዉ ከኮሚሽኑ ቀልጣፋ፣ ዉጤታማ እና ወጪ ቆጣቢ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ እና በከተማዋ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ የድርሻቸዉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ነዉ መማክርት ጉባኤ መመስረት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
የህዝቡን ቀጥተኛና ነጻ ተሳትፎ ለማጎልበት የሚያስችል ወጥነትና ግልጽነት ያለው የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት፣የአጋዥ አካላትን መንግስታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት ተሳትፎን ለማጎልበት የሚያስችል አሰራር ለመዘርጋት፣የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ በመፍጠር በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ከተገልጋይ ጋር በቅንጅት በመለየት ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመፍታት፣በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ተግባራት ላይ የዜጋውን አቅም እና እውቀት በተገቢው መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል የሰነዱ ዓላማ እንደሆነ አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስለሽ ወርቅነህ በሰነዱ ላይ አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም የከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ም/ክ ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር ) እና የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበበ ከተሳታፊዎቹ ለተነሱት ሀሳብና አስተያየት ምላሽ በመስጠት የምስረታ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments