በዓሉ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራላዊ ሥርዐት ማእቀፍ የተገነባ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ሥር እንዲሰድ ያደርጋል፡፡
በዓሉ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራላዊ ሥርዐት ማእቀፍ የተገነባ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ሥር እንዲሰድ ያደርጋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን "ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ-ቃል ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ከአመራሮቹና ጠቅላላ ሰራተኞች ጋር አከበረ፡፡
"ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የ20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በማስመልከት በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ፌዴራላዊ ሥርዐት ማእቀፍ የተገነባ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር ሰፊ የአስተምሮ ሥራ ለመሥራት እድል ይፈጥራል (አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስለሽ ወርቅነህ)።
ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ዴሞክራሲ እንደ መንግስት አስተዳደር የሚገለፀዉ በዉክልና እንደሆነ ገልጸው በህገ-መንግስቱ ላይ ጥያቄ ያለው ሰው ለምክክር ኮሚሽኑ ሀሳቡን በጽሁፍ እንዲሰጥ መንግስት በሩን ክፍት አድርጓል ብለዋል፡፡
ዴሞክራሲ እንደ ባህል የኑሮ ዘይቤ አንዱ የባህል መገለጫ ፣የፖለቲካ ባህል ፣አንድ ማሕበረሰብ በአገሩ የፖለቲካ ጉዳዩች ላይ ያለዉን እምነት፤ ስሜት እና አስተሳሰብ የሚያጠቃልል ነዉ (አቶ ጌታሁን አበበ የጽ/ቤት ኃላፊ)፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments