በከተማ ግብርና ዘርፍ የእፅዋት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ከክፍለከተማ ቡድን መሪዎች ጋር ሪፖርት ገመገመ፡፡
በከተማ ግብርና ዘርፍ የእፅዋት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ከክፍለከተማ ቡድን መሪዎች ጋር ሪፖርት ገመገመ፡፡
አዲስ አበባ፤ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም
የግብርና ኤክስቴንሽን ሥራ በመደበኛና በንቅናቄ ሰራ መቆየቱ፤ምርትና ምርታማነትን ሊጨምሩ የሚችሉ የምርት ማሳደጊያ ቴክኖሎጂዎች መቀረጻቸው፤ድህረ-ምርት አያያዝና ሥርዓተ ምግብን መሠረት ያደረገ ተግባር የድሃ ድሃ በሆኑ ተጠቃሚዎች ላይ መሰራቱ በአራት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራቶች ናቸው፡፡
በወንዝ ዳርቻ እና በኮሪደር ልማት የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ ፣አዋጭ የቴክኖሎጂ አማራጭን ማፈላለግ ስልጠና ማመቻቸት፣የተሰሩ የምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት ለመቀመር እና ለማስፋፋት መረጃ በማደራጀት፣ ለልማት ለሚነሱ አርሶ አደሮች የካሳ ግምት ክፍያ የሚሆን የምርት ግምት ትንተና ጥናት ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መሠራቱ ከእቅድ ዉጪ የተከናወኑ ተግባራቶች ናቸው፡፡
የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠሉ እና ከአከባቢ ጥበቃ ጋር በመሆን ስልጠና መሰጠቱ በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች ሲሆኑ መረጃ አያያዝ ክፍተት መኖሩ የሪፖርት ጥራት ጉድለት መኖሩ በክፍተት የታዩ ጎኖች እንደሆኑ የ4 ወር ሪፖርት ግምገማ ባካሄዱ ወቅት አንስተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments