የተፋጠነ  ዘመናዊ  የሰብል  ምርት  አሰባሰብ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የተፋጠነ  ዘመናዊ  የሰብል  ምርት  አሰባሰብ  ዘዴ  ብክነትን  ያስወግዳል፡፡

የተፋጠነ  ዘመናዊ  የሰብል  ምርት  አሰባሰብ  ዘዴ  ብክነትን  ያስወግዳል፡፡


አዲስ አበባ፤ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም


የተፋጠነ  ዘመናዊ  የሰብል  ምርት  አሰባሰብ  ዘዴ  ብክነትን  የሚቀርፍ፣ ቀጣይ ልማትን የሚያሳልጥ ነው፡፡በመሆኑም ለአብዛኛው አርሶ  አደሮች  ብሎም  የሀገራችን አካባቢ ልዩ ትርጉም ያለው የመኸር ወቅት  አርሶ አደሩ የአመት ልፋቱን፣ የድካሙን ዋጋ የሚሰበስብበት ወሳኝና ልዩ ትኩረት የሚሻ ጊዜ እንደሆነ ይታወቃል ። 


ያም ሆኖ የሀገራችን የግብርና ዘርፍ  አለመዘመን  መገለጫ  በሆነው  ሗላ  ቀር  የምርት  አሰባሰብ  ሂደትና  ትኩረት ማነስ ምክንያት  አርሶ  አደራችን  የጥረቱን  ያክል  እንዳያገኝ  ሲያደርገው  ቆይቷል። 
በተለይም  ደግሞ  በድህረ  ምርት ወቅት  የሚታየው ከፍተኛ  ብክነትና  የምርት  ጥራት  መቀነስ  እንዲሁም  ወቅቱን  ባልጠበቀ  ዝናብ  ምክንያት የሚከሰተው  የሰብል  ምርት  ብልሽት የግብርናው ዘርፍ አሳሳቢ ችግሮች ሆነው ቆይተዋል ።


ለእነዚህ ችግሮች ቁልፉ  መፍትሄ የደረሱ ሰብሎችን ፈጥኖ መሰብሰብ  በተለይም ደግሞ የግብርና ሜካናይዜሽንን በመተግበር  በዘርፉ  ቴክኖሎጂ  የተደገፈ ዘመናዊ የምርት  አሰባሰብ  ዘዴን  መጠቀም ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments