በመካከለኛ ዘመን የወጭ ማዕቀፍ ዝግጅት ዙሪያ  ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

በመካከለኛ ዘመን የወጭ ማዕቀፍ ዝግጅት ዙሪያ  አመራርና ባለሙያዎች ጋር ውይይት

አዲስ አበባ፤ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን  በመካከለኛ ዘመን የወጭ ማዕቀፍ ዝግጅት ዙሪያ  አመራርና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

በአግባቡ  የተተገበረ  የወጭ  ማእቀፍ፡- በወጭና ገቢ መካከል ሚዛናዊ  ሁኔታ  እንዲፈጠር  ይረዳል፣በከተማው የበጀት አመዳደብ ላግልጸኝነትን ያሰፍናል፣በአስፈጻሚ አካላት ዘንድ ፍትሀው የበጀት ድልድል እንዲኖርና አጠቃቀማቸው እንዲያድግ በቀጣይ  ዓመታትም  የሚመደብላቸውን በጀት እንዲውያቁ እና አዳዲስ ፖሊሲዎች  ሲዘጋጁ የፊዚካል ተጽኖ ቀድሞ በመገንዘብ እርምጃ ለመውሰድ የሚረዳ መሳሪያ እንደሆነ  የዕቅድ፣ በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት  ባለሙያ  ወ/ሮ  ፀደይ  አለነ  በሰነዱ  ላይ  አንስተዋል፡፡

የካፒታል  በጀት ለማዘጋጀት በቅድሚ የሴክተሩን፣ፕሮግራሞችንና የፕሮጀክቶች ፣ከመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች አፈጻጸም  አኳያ ያላቸውን ድርሻ  መገምገም   የካፒታል በጀት ዝግጅት  መርሆች  እንደሆኑ  የዕቅድ፣ በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር በላይ ነህ ቢሻው  ገልጸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments