የሙያዊ   ሥነ-ምግባር  ክፍተት የፍትህ መጓደል...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የሙያዊ   ሥነ-ምግባር  ክፍተት የፍትህ መጓደልን ያስከትላል፡፡

የሙያዊ   ሥነ-ምግባር  ክፍተት የፍትህ መጓደልን ያስከትላል፡፡


አዲስ አበባ፤ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም


በዓለም አቀፍ ለ22ኛ ጊዜ  በሐገራችን ለ21ኛ ጊዜ ትውልድን  በሥነ-ምግባር፤ተቋምን በአሰራር ! በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ   የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡ 

በአዲስ አበባና ከተማ አስተዳደር አርሶ አርሶ  አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረው የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ  በሙያዊ   ሥነ-ምግባር ዙሪያ   ዳይሬክተሮች፣ቡድን መሪዎችና  ከፍተኛ  ባለሙያዎች  ጋር  የፓናል  ውይይት  ያካሄደ ሲሆን  የሙያዊ   ሥነ-ምግባር  ክፍተት መኖሩ  የሚያደርሰው ጉዳትና መፍትሄዎቹ  በሚል ርዕሰ ጉዳይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ሥነ-ምግባር  ማለት  የአንድ  ሰው   ጥሩ ወይም  መትፎ ጎን  ውጤቱ  የሚለካበት  እንደሆነና  ከሞራልና አመለካከት አንጻር የሚገመገምበት እንደሆነ በውይይቱ ተነስቷል፡፡ስለሆነም የሥነ-ምግባር መጓደል አካባቢን፣ማህበረሰብን፣ኢኮኖሚን  እና ማህበራዊ ኑሮን  እንደሚጎዳ  ተወያዮቹ አንስተዋል፡፡
በማህበረሰቡ ዘንድ   በተደጋጋሚ  ግንዛቤን መፍጠር፣ጠንካራ የህግ ማእቀፍ መዘርጋት እና ተጠያቂነትን  ማስፈን  የሥነ-ምግባር መጓደልን  ማስተካከል እንደሚቻል ተብራርቷል፡፡

በመጨረሻም  ከተሳታፊዎቹ  ለተነሱት  ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments