ሙስና በማህበረሰቡ ቀደምት ብሂሎች ውግዝ ነው።
ሙስና በማህበረሰቡ ቀደምት ብሂሎች ውግዝ ነው።
አዲስ አበባ፤ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛው ጊዜ በሀገር አቀፍ ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን በዓል "ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል ከአመራሮችና ጠቅላላ ሰራተኞች ጋር የፓናል ውይይት አኳሂዷል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ሙስና ዘርፈ ብዙ መገለጫ ያለው ኢ-ሞራላዊ ተግባር በመሆኑ ግለሰብን፣ ማህበረሰብን፣ ተቋምን ብሎም ሀገርን በእጅጉ የሚጎዳ ስለሆነ ሁላችንም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በመፀየፍ፣ በመታገል እና በመከላከል የበኩላችንን ሚና መወጣት ይገባል ብለዋል፡፡
በአለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት “ሙስና” መቅሰፍት ነው። ጥፉት፣ ብልሹ፣ ግም፣ መበስበስ፤ መከራ”... እና በመሰል ነውርን በሚገልጡ ቃላት ይፈቱታል። ሙስና በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ኃጢያት፣ በዓለማዊ ሕጎች ወንጀል የሆነ በማህበረሰቡ ቀደምት ብሂሎች ውግዝ ነው።
ኦክስፎርድ መዝገበቃላትም ሙስናን (Corruption) ከአለመታመን/እምነትን ከማጉደል፣ ምግባረ ቢስነት፣ ጉበኝነት እና በመሰል ቃላት ይገልፀዋል። ከዝቅጠትና ከመቆርቆዝ ጋር ያቆራኘዋል።
በመሆኑም ሙስና የማህበረሰቡን የሞራል፣ የሕግና ፍትሕ እሴቶች ይንዳል፤ የፖለቲካ ብክለት መገለጫ ነው፤ የነባር ግብረ ገባዊ እሴቶች መናድ ማሳያ ነው፤ ለማኅበረሰብ ሕልውና አደጋ ነው፡፡
ሌላው ሙስና ምቾት፣ ቅምጥልነትና ራስ ወዳድነት መንፈስ የተጠናወተው እኩይ ምግባር መላበስ ነው። በጥቂቶች ብዙሃኑን የሚበክል ድርጊት ነው። እናም ኢ-ፍትሐዊነት፣ የግል ጥቅም አሳዳጅነት፣ ሥርዓተ አልበኝነት፣ አድልዎ እና የሞራል ዝቅጠት እንዲለመድ ያደርጋል።
ሙስና ድህነትን ያባበሳል፤ ሰብዓዊ መብትና ክብርን ይገፋል፤ የዳበረ ባህልን ይሸረሽራል፤ ዕድገትን ይጎትታል፤ ግጭት ይቀሰቅሳል፤ የመንግስትን ቅቡልነት እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን ይፈታተናል።
የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መርጋ ጢጣ ሙስና በተለያየ መልኩ ሊተገበር የሚችል ብልሹ ተግባር በመሆኑ እንደ ኮሚሽን በተለይም ለሌብነትና ብልሹ አሰራር ተጋለጭ ናቸው ተብለው በተለዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
አያይዘውም የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች የትኛውንም ዓይነት የሌብነትና ብልሹ አሰራር ተግባርና ዝንባሌዎች ስትመለከቱ ጥቆማ ብትሰጡን አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ የምናደርግ ይሆናል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ መልኩ ምንም ይሁን ምን ሙስና ጠንክሮ መስራትን የሚኮንን፣ ሳይሰሩ መብንላትን የሚያጀግን፣ የአጋርነትን ሞራል የሚሰብር፣ ሀገርን ለደህንነት ስጋት አደጋ የሚጥል፣ ኢንቨስትመንትን የሚያቀጭጭ፣ መረጋጋትን የሚፈትን፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና ዘላቂ ልማትን የሚገታ በመሆኑ ከእያንዳንዳችን የሚጠበቀውን ተግባር በመፈፀም የተግባር ሰው ሆነን መገኘት አለብን በማለት አጽህኖት ሰጥተው ተናግረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments