አርሶ አደሩ ከከተማዋ ልማት ጋር አብሮ እንዲለማ...

image description
- In አርሶ አደር ልማትና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ    0

አርሶ አደሩ ከከተማዋ ልማት ጋር አብሮ እንዲለማ እየተሰራ ይገኛል፡፡

አርሶ አደሩ ከከተማዋ ልማት ጋር አብሮ እንዲለማ እየተሰራ ይገኛል፡፡


አዲስ አበባ፤ ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም



አርሶ አደሮች ወደ ኢንቨስትመንት ገብተው ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ በኮሚሽኑ በኩል አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆን የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በመገኘት ምልከታ አድርገናል፡፡


በምልከታችንም የአቶ ከተማ መንግስቱ፣ አቶ አለማዬሁ ጉልማ እና አቶ መኮንን አሰፋን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተናል፡፡


አቶ መኮንን አሰፋ ትምህርት ቤት ሰርተው ለመንግስት በማከራየት በወር ከ900,000 ያላነሰ ገቢ እንደሚያገኙ፣ ግሮሰሪ፣ የዶሮ እርባታ፣ የከብት ማድለብ፣ የወተት ላም እርባታ ላይ ተሰማርተው ከ41 በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደፈጠሩም ገልፀውልናል፡፡


ሌላው አቶ መኮንን ከ3,000 በላይ ዶሮ እያረቡ ሲሆን በቀን ከ2,600 በላይ እንቁላል እንደሚያገኝ፣ አንድ እንቁላል በ17 ብር እንደሚሸጥ እንዲሁም ወተት ለአካባቢው ማህበረሰብ 90 በሊትር እያቀረበ እንደሆነ ገልጿል፡፡
በመስክ ድጋፍ ላይ ያገኘናቸው ኮሚሽኑ እና የክፍለ ከተማ ባለሙያዎች አርሶ አደሩ ወደ ኢንቨስትመንት በመግባት ከራሱ አልፎ ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የሚጠበቅብንን ሁሉ እያደረግን ነው ብለዋል፡፡


አርሶ አደሩ ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገባ ከማድረግ ጋር ምን እየተሰራ እንደሆነ ያነጋገርናቸው የአርሶ አደር ልማት ቡድን መሪ ወ/ሮ ደግነሽ በደዊ ከ152 በላይ አርሶ አደሮች ለኢንቨስትመንት ሁኔታዎች እንደተመቻቸላቸው፣ 58ቱ በራሳቸው እና በኮሚሽኑ ድጋፍ ወደ ሥራ እንደገቡ ገልፀዋል፡፡


አያይዘውም የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ፣ ሙያዊና ቴክኒካል ድጋፍ የመስጠት፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሮቻቸው እንዲፈቱ የማድረግ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡
የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሣ ባይሣ ቀደም ብሎ አርሶ አደሮች ወደ ኢንቨስትመንት ለመግባት አስበው ጥያቄ ሲያቀርቡ የሚቀርቡላቸው ምርጫዎች ሦስት ብቻ ስለነበሩ እጅግ በጣም ሰፊ ችግር ነበረብን አሁን ላይ ከፕላንና ልማት ቢሮ ጋር በመነጋገር ከ18 በላይ ዘርፎች ፀድቀው በመምጣታቸው የተሻለ ነገር አለ ብለዋል፡፡


አቶ ረጋሣ ድጋፍ ከማድረግም ጋር በተያያዘ አርሶ አደሮቹን በመስክ በመገኘት፣ ቅንጅታዊ ተቋማት ጋ ቢሯቸው ድረስ በመሄድ፣ የሙያና የቴክኒክ ምክርና ድጋፍ በመስጠት፣ ግንዛቤና ስልጠና በመስጠት አርሶ አደሮቹ ወደ ኢንቨስትመንት ገብተው ከከተማዋ ጋር አብረው እንዲለሙ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments