ስልጠና የሰራተኛውን አቅም ከመገንባት ባሻገር ሚናው ዘርፈ ብዙ ነው።
ስልጠና የሰራተኛውን አቅም ከመገንባት ባሻገር ሚናው ዘርፈ ብዙ ነው።
አዲስ አበባ፤ ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ለሰራተኞቹ የአቅም ግንባት ስልጠና ሰጥቷል።
የማዕከሉ ሰራተኞች በዕቅድ ዝግጅት ሂደት፣ በBSC እና በKPI አተገባበር፣ በዕቅድ ካስኬዲንግ፣ በሪፖርት ዝግጅት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በውሎ ምዝገባ፣ በሥነ-ግባር፣ በሙስና መከላከያ መንገዶች እና ተያያዥ ይዘቶች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።
ሰራተኞቹ በተሰጠው ስልጠና ላይ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
አቶ ስለሽ ወርቅነህ፣ አቶ መርጋ ጢጣና አቶ ወንደሰን አካሌ ስልጠናውን ከኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴትና አጠቃላይ የሥራ አፈፃፀም ጋር በማስተሳሰር አቅርበዋል።
የተሰጠው ስልጠና ለሰልጣኞች አቅም ከመገንባት ባሻገር መነቃቃትን የሚፈጥር መሆኑም በስልጠናው ወቅት በሰልጣኞች ተነስቷል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments