በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የዜጎ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የዜጎችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል - ኮሚሽኑ

በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የዜጎችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል - ኮሚሽኑ


አዲስ አበባ፤ ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም


በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የዜጎችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን  የአስተዳደሩ የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ የከተማ ግብርና አሁን ላይ በስፋት ተደራሽ መሆን በመቻሉ ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ፍጆታ ከመሸፈን ባለፈ ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ ገቢያቸውን ማሳደግ ችለዋል።

በመዲናዋ በከተማ ግብርና በተለይ በሰብልና በእንስሳት ሀብት ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ለኢዜአ እንደገለጹት የከተማ ግብርና ከተጀመረ ወዲህ ምርታቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እያቀረቡ ነው፡፡

መንግስት ለግብርና ስራ የሚያስፈልጉ ምርጥ ዘር፣ ጸረ ተባይ፣ የባለሙያ እገዛ እና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ የተለያዩ ድጋፎች እያደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ በግብርና ሥራ የተሰማራው ወጣት ታቦር ከበበ አሁን ላይ ከራሱ የእለት ፍጆታ ባለፈ ምርቱን  በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እያቀረበ መሆኑን ተናግሯል።

በከተማ ግብርና ከተሰማራበት ጊዜ አንስቶ በኮሚሽኑ በተደረገለት ድጋፍ ኑሮውን በማሻሻል ተጠቃሚ መሆኑን የተናገረው ደግሞ እሸቴ ገመቹ ነው፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪው ደበበ ቢራቱ በተመቻቸላቸው የከተማ ግብርና እድል የተለያዩ የሰብል ምርቶችን በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ 

አቶ ቢራቱ ሆርዶፋ በበኩላቸው እንስሳትን በማድለብና የተለያዩ የሰብል ምርቶችን ለገበያ እያቀረቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የመዲናዋ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ እንደገለጹት፤ የከተማ ግብርና የመዲናዋን አርሶ አደሮች ጨምሮ የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየቀየረ ነው።

የከተማ ግብርና የህብረተሰቡን የእለት ፍጆታ ከመሸፈን ባለፈ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments