የማዕከሉ ሠራተኞችና ባለሙያዎችን ለማብቀት ተከታ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

የማዕከሉ ሠራተኞችና ባለሙያዎችን ለማብቀት ተከታታይ ሥልጠናዎች እየተሰጡ ነው።

የማዕከሉ ሠራተኞችና ባለሙያዎችን ለማብቀት ተከታታይ ሥልጠናዎች እየተሰጡ ነው።
እ/ል/ል/ማ፤ አዲስ አበባ (ህዳር 19/2018 ዓ.ም)
===
በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ውስጥ ያሉ ሠራተኞችንና ባለሙያዎችን ለማብቃት ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች እየተሰጡ ነው።
በዛሬው ዕለትም በሦስት ክፍሎች ሥልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን የመጀመሪያውን ክፍል በኮሚሽኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አካሌ ሰጥተዋል። በዚህ ክፍል በዕቅድ አስተቃቀድ፣  በBSC፣ KPI እና በሪፖርት አደራረግ ዙሪያ በቂ የሆነ ውይይት ተደርጓል።
የሁለተኛውን ክፍል ሥልጠና የሰጡት የኮሚሽኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ስለሺ ወርቅነህ በተቋምና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለተሳታፊዎች በቂ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል።
የመጨረሻውን ክፍል ሥልጠና የሰጡት ደግሞ የኮሚሽኑ የስነምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መርጋ ጢጣ በስነ ምግባርና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ከሙያና ሙያዊ ስነ ምግባር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ሥልጠና ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ከሥልጠናው ተሳታፊዎች በየሥልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሃሳብና አስተያየት ሰጥተው አሠልጣኞችም ምላሽ ሰጥተውበት ሥልጠናው ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments