በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ በወረዳ 11 እና 12
ሕዳር 20/2018 ዓ.ም
ከፍተኛ አመራሮቹ በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ በወረዳ 11 እና 12 በአካል ከቦታ ቦታ በመዘዋወር በመንግስት ካፒታል በጀትና በአርሶ አደሮች የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የተቀናጁ የከተማ ግብርናና ሌማት ቱሩፋት የደሮና የወተት ምርት ክላስተሮችን ተዘዋውረው በመጎብኘት አበረታትተዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና በበኩላቸው የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብር ስራዎች ለአካባቢው ነዋሪዎች ተጨማሪ ገቢ መፍጠር ከመቻላቸውም በላይ በአካባቢው ለሚገኙ የፍጆታ ዕቃዎችና ምርቶች አቅርቦት መሻሻል ምክንያት የዋጋ ንረትን ለመግታት እንደ አስተዳደር በሁሉም ወረዳዎች ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ለአመራሮቹ አብራርተዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራትም እንደ አስተዳደር በክፍለ ከተማው በዶሮና የወተት ላሞችን በክላስተር ወደስራ በማስገባት ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶችም የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
አመራሮቹ ስራዎቹን በቦታው ተገኝተው ከመመልከት በተጨማሪ በዶሮና በወተት ምርት አርሶ አደሮችን በማነጋገር ለቀጣይ ስራቸው የሚያበረታታ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በጉብኝቱ የተሳተፉ አመራሮች የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤን ጨምሮ የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት፣ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና ዳይሬክተሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት መካሻ፣ የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments